Home

ወ/ሮ ፋጡማ መሀመድ

የአሶሳ ከተማ አስተዳደር የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ሀላፊ

እንኳን ደህና መጣችሁ

በከተማችን በየደረጃው ላሉት ባለበጀት ተቋማትንና የተገልጋዮችን ፍላጐት በቀጣይነት ለማርካት  የባለፉት ሁለት አምስት ዓመታት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም፣ ሀገራዊና ክልላዊ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጅዎች እንዲሁም የትኩረት አቅጣጫዎችን መሠረት በማድረግ ተቋሙ የሚሰጣቸው በጀት የመደልደል፣ የከተማዊ ምጣኔ ሐብት ዕድገት ጥናት የማድረግ፣ የልማት አጋሮችንና የሥነ-ሕዝብ ጉዳዮችን የማስተባበር፣ የመንግስት ግዢና ንብረትን የማስተዳደር፣ የፋይናንስ አጠቃቀሞችን ኦዲት የማድረግ ሥራዎችን  የበለጠ  አጠናክሮ  በመሄድ  የከተማዉን ህዝብ የልማት ተጠቃሚነት ሊያረጋግጥ  በሚያስችል መልኩ የአንድ ዓመት ዕቅድ  ማዘጋጀት አስፈላጊ ሁኖ ተገኝቷል፡፡

በመሆኑም የተቋሙን ስትራቴጂያዊ ዕቅድ፣ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች፣የከተማ አስ/ር ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች የዕቅድ እና የሪፖርት ግብረ-መልስን መሠረት በማድረግ፣ የተቋሙን ያለፈውን ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም  ግምገማ  መነሻ  በማድረግ፣ ወቅታዊ የተገልጋኞች ፍላጐት መሰረት በማድረግ፣ ተቋሙ የሚሰጣቸውን አጠቃላይ አገልግሎቶችና የፋይናንስ አስተዳደራዊ ሥራዎችን በብቃት ለመወጣት  የሚያስችለውን  ዓመታዊ ዕቅድ  አዘጋጅቷል፡፡